Testimonials from different clients
ዶ/ር ብርሃኑ ስለ ባለቤቴ ገነት ህክምና በጣም አመሰግናለሁ በእዉነት ጥሩ ሀኪም ነህ።እግዚአብሔርን መፍራት፣ሙያና ስነምግባር ሲዋሃዱ ድንቅ ውጤት አላቸው።እኔና ባለቤቴ መምህራኖች ነበርን በዚህች ሃገር መምህርና ሃኪም ብዙ ዋጋ እንደሚከፍሉ አውቄያለሁ።የመምህርን በራሴ የሃኪምን ደግሞ ባለቤቴን ሳስታምም አየሁት። በተለይ የህክምናውን ክፍያ ሳሰራና ለየአንዳንዳችሁ የሚደርሰውን በሃሳቤ ሳሰላው ገረመኝ በተጨማሪ ያለባችሁን ጭንቀት ሳስበው ከልቤ አዘንኩ የሰው ህይወትና ጤና ነውና በናንተ ላይ የወደቀው።ግን ደግሞ የመንፈስ እርካታችሁን ሳስበው በተለይ በአስቸጋሪ ስራ ውስጥ ታካሚያችሁ ከበሽታው ሲፈወስ ምንኛ እንደምትደሰቱ ሲታየኝ እግዚአብሔርን አመሰገንኩት።ሴቷ ልጄ የህክምና ሙያ በፍላጎቷ መርጣ መማር መጀመሯ አስደሰተኝ።እኔ 30 ዓመት አስተምሬያለሁ ካጣሁት ገንዘብ ይልቅ ያፈራኋቸውን ተማሪዎቼን ሳገኝና የደረሱበትን ሳውቅ ትልቅ እርካታ ይሰማኛል።
እኛ እዚሁ ቀዶ ጥገናውን ለማድረግ እንድንወስን ስለረዳኸንና ለባለቤቴ የተሳካ ቀዶ ጥገና ስላደረክላት አመሰግንሃለሁ አከብርሃለሁ እግዚአብሔር ይስጥልኝ እላለሁ።
መልከሙን ሁሉ እግዚአብሔር ያድልህ
መቅድም
Total Page Visits: 529 - Today Page Visits: 2