ራሴን አመመኝ የማይል ማን አለ?…ይነስም ይብዛ፡፡ የሕመም ማስታገሻ እየቃሙ የሚኖሩ አያሌ ናቸው፡፡ ሻሽ ጠምጥመው የሚዉሉ ቤት ይቁጠራቸው፡፡ ቂቤ አናታቸው ላይ አኑረው ከራሳቸው ጋር ሰላም ለመፍጠር የሚፈልጉ እመቤቶችም ብዙ ናቸው፡፡ እስኪ ስለራስ ሕመም አንዳንድ ነጥቦችን እናውጋ፡፡
የራስ ምታት በጭንቅላት ወይም ማጅራት ላይ የሚጠያጋጥም ከቀላል እስከ ከባድ ህመም የሚያስከትል የተለመደ ደዌ ነው፡፡ ብዙዎቻችን የራስ ሕመምን አንድ አይነት አድርገን እናስበው እንጂ በታለያዩ ምክንያቶች የሚነሱና የተለያዩ የህመም ምልክቶች ያሏቸው የራስ ምታት ኣይነቶች እንዳሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ምንም እንኳን የበረታ የህመም ስሜትና ምቾት ማጣትን ብሎም ብስጭትን ቢፈጥሩም፣ ብዙዎቹ የራስ ምታት ዓይነቶች የከባድ ችግር መገለጫ አይደሉም፡፡
ሁልጊዜም የሚያጋጥም ችግር ካልሆነ በቀር በቀላል የህመም ማስታገሻ እና አኗኗራችንን በማስተካከል ህመሙን ማስታገስ ይቻላል፡፡
መነሻ ምክንያቱ ምንድን ነው?
የራስ ምታት በተለያየ ምክንያት ሊነሳ ይችላል፡፡ ከነዚህም ውስጥ አብዛኞቹን በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች መመደብ ይቻላል፡፡
ይህ ከሁሉም የራስ ምታት ዓይነቶች በአብዛኛው የሚከሰተው እና ጾታ ሳይለይ ወጣት እና ጎልማሶችን የሚያጠቃ ሲሆን በጭንቅላት እና አንገት ጡንቻዎች መኮማተር ምክንያት ይነሳል፡፡
የውጥረት ራስ ምታት አልፎ አልፎ የሚከሰት ቢሆንም አንዳንድ ሰዎች ላይ ግን እየተደጋገመባቸው ሊሰቃዩ ይችላሉ፤፤
መነሻውም ፡-
የሚግሬይን ዋነኛ መነሾ ባታወቅም ብዙ መላ ምቶች ግን አሉ፡፡ ከነዚህ መላ ምቶች አንዱ በነርቭ ፤ ደም ቧንቧ እና አእምሮ ውስጥ በሚፈጠሩ ውስብስብ ለውጦች ይነሳል የሚለው ነው፡፡ ብዙ የሚግሬይን ዓይነቶች ቢኖሩም በራስ አንድ ጎን በኩል የሚሰማ ጠንከር ያለ የራስ ምታት እንዲሁም በብርሃን፣ በመጥፎ ጠረን ወይም ድምጽ መረበሽ መነሾ የሚቀሰቀስ ራስ ምታት የሚግሬይን ራስምታት ሊሆን ይችላል፡፡
ከብዙ የሚግሬይን ዓይነቶች ውስጥ ዋነኞቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
ይህ አይነቱ ራስ ምታት ገራገር ነው ሊባል ይችላል፡፡ ምክንያቱም ችግሩ ከመከሰቱ በፊት ጥቆማ ይሰጣል፡፡ በዚህ ችግር ከሚጠቁ ሰዎች ከሦስቱ በአንዱ ባለ ቅድመ ምልክት ሚግሬይን ተጠቂ ነው፡፡ ይህም ማለት ራስ ምታቱ ከመጀመሩ አስቀድሞ የማስጠንቀቂያ ምልክቶችን የሚያሳየው የሚግሬይን ዓይነት ያጋጥመዋል፡፡ ቅድመ-ምልክቶቹ ምን ሊሆኑ ይችላሉ? ብልጭ ብሎ የሚጠፋ የብርሃን ዓይነት መታየት፤ የዕይታ ለውጥ ፤ አንገትን ወይም ማጅራትን መጨምደድ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ምንም እንኳን ሚግሬን የራስ ምታት ዓይነት ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ቀደም ሲል የተጠቀሱት ቅድመ-ምልክቶች እያሉዋቸው ራስ ምታት ላይኖራቸው ይችላል፡፡ ምክንያቱ ብዙም ግልጽ ባልሆነ መልኩ ሚግሬይን ከወንዶች ይልቅ በአብዛኛው ሴቶችን ያጠቃል፡፡ ባስ ሲልም የተጠቂውን የቀን ተቀን እንቅስቃሴ ሊያውክ ይችላል፡፡
የሚከተሉት ከሚግሬይን መከሰት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ምክንያቶች ናቸው፡-
ሚግሬይን በዘር የሚወረስ ደዌ ነው፡፡ ከወላጆች አንዱ በሚግሬይን ተጠቂ ከሆነ ልጆች ላይ ሊስተዋል ይችላል፡፡
ሚግሬይንን የሚያስነሳ ኬሚካል ይይዛሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ሌላ ጥናት ደግሞ ከሚግሬይን መጀመሪያ ምልክቶች ውስጥ አንዱ እነዚሁኑ ምግቦች መናፈቅ ነው ይላል፡፡
የውጥረት እና ሚግሬይን ራስ ምታት ልዩነቶች
የዉጥረት ራስ ምታት ህመሙ በአንድ ጎን ብቻ ከመሆን ይልቅ በጠቅላላው ራስ እና አንገት ዙሪያ ይሆናል፡፡ ህመሙ ራስ እና ማጅራትን ወጥሮ የሚይዝም ሊሆን ሲችል ከሚግርይን ጋር ሲነጻጸር በጊዜ መድኃኒት ከተወሰደበት ለአጭር ግዜ ብቻ የሚቆይ ነው፡፡ የሚግሬይን ራስ ምታት ግን በአብዛኛው አምስት ደረጃዎችን ያልፋል፡፡
እነዚህም፡-
ህክምና የሚያስፈልገው መቼ ነው?
አልፎ አልፎ የሚከሰት ራስ ምታትን ያለ ሃኪም ትዛዝ ሊወሰዱ በሚችሉ ቀላል የህመም ማስታገሻዎች አሊያም በእንቅልፍ እና ራስን ዘና በማድረግ፣ መጠነኛ እረፍት ለራስ በመስጠት ማሻሻል ይቻላል፡፡ ህመሙ በተደጋጋገሚ የሚከሰት ከሆነ ግን መንስኤውን ለማወቅ ሀኪም ማማከር ያስፈልጋል፡፡
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ምልክቶች ከተንፀባረቁ በፍጥነት ሃኪም ቤት መሄድ ያስፈልጋል፡-
ሀኪሞች ምርመራውን እንዴት ያከናውናሉ?
የህመምተኛውን የህመም ታሪክ፤ የቤተሰብ ሁኔታ፤ አመጋገብ እና አኗኗር ማወቅ ሀኪሙ ቀጣይ ማድረግ ያለበትን ምርመራ እና መፍትሄውን እንዲወስን ይረዳዋል፡፡
ሀኪሙ ስለ ራስ ምታቱ ቆይታ ፤ ዓይነት ፤ ተዛማጅ ችግሮች እና ምክንያቶች ይጠይቃል፡፡ ብዙ የራስ ምታት ዓይነቶች (ረጅም ግዜ የሚቆዩትን ጨምሮ) ለከፋ አደጋ የማያጋልጡ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን የማያቋርጥ እና ከባድ ከሆነ የሚከተሉት የባለሙያ ምርመራዎች ሊታዘዙ ይችላሉ፡፡
ህክምናው ምንድን ነው?
ሀኪሙ የህመሙን መነሻ እና ማድረግ ያለበትን የምርመራ ዓይነቶች እና ሕክምና ለመወሰን እንዲረዳው ህመምተኛው በቀን መቁጠሪያ ወይንም ማስታወሻ ደብተር ላይ ህመሙ የጀመረበትን ሰዓት፣ ምን ያህል እንደቆየ እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን እንዲያሰፍር ሊጠይቀው ይችላል፡፡ ማስታወሻውን በቀጣይነት ከአንድ እስከ ሁለት ወራት በማቆየት ራስ ምታቱ በጀመረ ሰዓት የተወሰደውን ምግብ፣ መጠጥ፣ መድኃኒት፣ የአየር ሁኔታ፣ የቀን ተቀን እንቅስቃሴዎች ውስጥ ያሉ ጫናዎች እንዲሁም ሴቶች በወር አበባ ወቅት የሚሰማቸው ስሜት ወዘተ በመመዝገብ ህመሙን የሚያስነሱ ምክንያቶችን ለማወቅ እና ለማስቀረት ይረዳል፡፡
የህክምናው ዓይነት ከሰው ሰው ቢለያይም በአብዛኛው ግን እንደ ፓራሲታሞል፣ አስፕሪን እና አይቦፕሮፌን በመሳሰሉ ህመም ማስታገሻዎች መፍትሄ ማግኘት ይቻላል፡፡ እንደ ሚግሬይን ባለ ከባድ ራስ ምታት ጊዜም ቢሆን መጀመሪያ ህመሙን የሚያስነሱ ምክንያቶችን መረዳት እና ማስወገድ ቢቀድምም በሐኪም ትዕዛዝ የሚገኙ መድኃኒቶችን በመውሰድ ከድንገተኛ ራስ ምታት መዳን ይቻላል፡፡
ህክምናውን ህመሙ ከመባባሱ በፊት ቀለል ባሉ ፓራሲታሞል እና አይቦፕሮፌን በመሳሰሉ በውስጣቸው የሳዚሊን መድኃኒትን በሚይዙ ፈሳሻ የህመም ማስታገሻዎች መጀመር እና በነዚህ መፍትሄ ካልተገኘ ግን በሀኪም ትዕዛዝ ብቻ ሚወሰዱትን ትሪፕታንስ የተሰኙትን መድኃኒቶች መዉሰድ ይኖርበታል፡፡ ሱማትሪፕታን ወይንም ዞልሚትሪፕታን የተሰኙት የትሪፕታን ዓይነቶች በሚግሬን የተነሳ ለውጥ የሚታይባቸው የደም ቧንቧዎች ላይ በመስራት ህመምን ያስታግሳሉ፡፡
ሱማትሪፕታን በአሁኑ ግዜ ያለሀኪም ትዕዛዝ ለመውሰድ የተፈቀደ ቢሆንም የትሪፕታን መድኃኒት ለሁሉም ሰው ላይሰራ እንደሚችል
ኒስ የተሰኘው ተቋም በቅርቡ ቲ.ኤም.ኤስ (TMS) የተሰኘውን የማግኔታዊ ምት የሚረቸውን አነስተኛ የኤሌክትሪክ መሳሪያ ጭንቅላት ላይ በእጅ በመያዝ የሚደረግ ህክምና በስራ ላይ እንዲውል ፈቅዷል፡፡ ምንም እንኳን ቲ.ኤም.ኤስ እንዴት እንደሚሰራ በውል ባይታወቅም ህመምን እንደሚቀንስ ግን ታምኖበታል፡፡
ቶሎ ቶሎ በሚግሬይን የሚሰቃዩ ሰዎች በስፔሺያሊስት ህክምና ሊረዱ ይችላሉ፡፡ ስፔሺያሊስቱም ፕሮፕራኖሎል እና አሚትሪፕታይሊን የተሰኙ ቤታ ብሎከር መድኃኒቶችን አሊያም ደግሞ “የሚጥል በሽታ” ላለባቸው ሰዎች የሚታዘዘውን እንደ ሶዲየም ቫልፕሮየት ዓይነት አንቲ – ኮንቨልሳንት መድኃኒቶችን ሊያዝ ይችላል፡፡
የጨጓራ በሽተኛ የሆኑ ሰዎች እንደ አይቦፕሮፌን ያሉ ኤን.ኤስ.ኤ.ዲ.ኤስ (NSADS) እና እንደ አስፕሪን ያሉ አሴታይሊሳይሊክ አሲድ (acetylsalicylic acid) መድኃኒቶችን መጠቀም ለምግብ መውረጃ ትቦ መድማት ሊያጋልጣቸው ስለሚችል ከዚህ መቆጠብ ይኖርባቸዋል፡፡
ያስተውሱ፡- ሐኪም ካላዘዘ በስተቀር ከ 16 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች አስፕሪን መሰጠት የለበትም፡፡
ራስዎን ለመርዳት ምን ማድረግ ይችላሉ?
በሐኪም በተደረገ ምርመራ ምንም ችግር ሳይገኝብዎ የራስ ህመምዎ ከቀጠለ የሚከተሉትን ምክሮች ልብ ይበሉ፡-
ሚግሬይን የሚያማቸው ሰዎች ፀጥ ባለ እና ብርሃን በሌለው ክፍል ውስጥ ማረፍ እና ህመማቸውን የሚያስነሱባቸውን የምግብ ዓይነቶችንም ሆነ ሌሎች ነገሮችን አለመጠቀም ወይንም ማስወገድ ስቃያቸውን ሊቀንስላቸው ይችላል፡፡