የወር አበባ ህመም

ዳይስሜኖሪያ በማህጸን ውስጥ በሚፈጠር መኮማተር የተነሳ የሚፈጠረው የወር አበባ ህመም በጣም አድካሚ እና የመጎተት ስሜት ያለው ነው፡፡ የቤት ውስጥ ህክምና በአሜሪካ ውስጥ በተደረገ ጥናት መሰረት ሙቅ ውኃ ሆድ አካባቢ መያዝ አይቦፕሮፌን ከመዋጥ ያልተናነሰ ውጤታማነት አለው፡፡ ሌላው በቤት ውስጥ ማዘጋጀት የምንችለው መድኃኒት ደግሞ አንድ እጅ የሚሆን ጦስኝ ቀዝቃዛ ወይንም የፈላ ውኃ ውስጥ ከ 5-7 ደቂቃ ነክሮ አቆይቶ መጠጣት ነው፡፡ ያለሀኪም ትእዛዝ መወሰድ የሚችሉ መድኃኒቶች በቅርቡ በኒውዚላንድ በተደረገ ጥናት አይቦፕሮፌን ከፓራሴታሞል የተሻለ የወር አበባ ህመም ማስታገሻ መሆኑ ተገልጧል፡፡ በሀኪም ትእዛዝ የሚወሰዱ መድኃኒቶች ጠንከር ያለ መድኃኒት ያስፈልግሻል? በጣም በባሰ ግዜ ሀኪም (የማህጸን ሀኪም) ህመም እና መንገብገብን የሚቀንሱ መድኃኒቶችን ሊያዝልሽ ይችላል፡፡ ለማንኛውም ሐኪም መጎብኘቱ ይመከራል፡፡

Total Page Visits: 856 - Today Page Visits: 2

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *