የአእምሮ ጤና መጓደል – የምንደብቀው ደዌ

By Dr Birhanu H.Michael (MD), Neurosurgeon, Asst. Professor in Neurological Surgeries, Chief of Spine Surgeries Unit

ከአምስት ሰው አንዱ በሕይወት ዘመኑ አንድ ግዜ የአእምሮ ጤና ችግር ይገጥመዋል፡፡ ብዙ ሰዎች ግን የሌሎች ሰዎችን ምላሽ በመፍራት ችግራቸውን በግልጽ አይናገሩትም፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ አሁንም ከአእምሮ ህመም ጋር የተያያዘ መጥፎ እሳቤ እና የግንዛቤ እጥረት አለ፡፡ ሌላው ቀርቶ በቤተሰብ እና በቅርብ ጓደኞች መሀል ስለሁኔታው መነጋገሩ እንደነውር ይታያል፡፡ ነገር ግን ይህ ሁሉም ሰው ላይ ሊደርስ የሚችል ነገር አንደመሆኑ አሳፋሪ ሊሆን አይገባም ይላል፡፡

በብዛት የሚታዩ የአእምሮ ጤና ችግሮች ምንድን ናቸው?

ዘጠኝ በመቶ የሚሆነው በአሜሪካና በታላቋ ብሪታኒያ የሚኖር የኅብረተሰብ ክፍል በአእምሮ ስጋት እና በጭንቀት ይሰቃያል፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንድ አራተኛ የሚሆኑት ብቻ ትክክለኛ የሀኪም እርዳታ ሲያገኙ ሌሎች ግን ሀኪም ጋር ሳይደርሱ በ18 ወራት ጊዜ ውስጥ ችግራቸው ይፈታል፡፡

የችግሩ ተጠቂዎች እነማን ናቸው?                  

ምንም እንኳን በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች፤ የረጅም ግዜ በሽታ ያለባቸው እና ስራ አጥ በመሆናቸው ከችግሩ ለመውጣት ቢቸገሩም ማንኛውም ሰው አእምሮ ጤና ችግር ሊያጋጥመው እንደሚችል ግን መገንዘብ ያሻል፡፡ ወደ ወጣትነት ዕድሜ በተጠጉ ቁጥር የመጠቃት ደረጃው ቢጨምርም ልጆችም  በአእምሮ በሽታ ሊያዙ ይችላሉ፡፡ ከ5-10 ዓመት እድሜ  የሆኑ ወንድ ልጆች 10.4 በመቶ  ከ11-15 ዓመት እድሜ  የሆኑ ወንድ ልጆች 12.8 በመቶ፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ ግን ዕድሜ በጨመረ ቁጥር እና ወደ መካከለኛ እድሜ አካባቢ በአእምሮ በሽታ የመያዝ ደረጃ እያደገ ይሄዳል፡፡

የመዘንጋት ደዌ (dementia)

ይህ ችግር ብዙ ግዜ በእርጅና ዘመን የሚያጋጥም ቢሆንም 15 ሺህ ያህል ሰዎች ግን ከ65 ዓመት እድሜ በታች ሆነውም ይታመማሉ፡፡ ብዙዎችም ተመርምረው ችግራቸውን ሳያውቁ ለብዙ ግዜ ይቆያሉ፡፡ የአልዛይመር እና ሌሎች የዴሜንሺያ ዓይነቶችን በጊዜ ለይቶ ለማወቅ አስቸጋሪ መሆኑን የአልዛይመር ጥናት ተቋሙ ዶ/ር ሜሪ ጄንሰን ያስረዳሉ፡፡ ቢሆንም ግን በተቋሙ ያሉ ሳይንቲስቶች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የማስታዎስ ችሎታ ምርመራ ፤ የአንጎል ስካን ፤ ሬቲና የተባለው የአይን ክፍል ምርመራ የመሳሰሉትን በማድረግ በሽታውን ለመከላከል እና ለማከም የሚረዱ አዲስ ግኝቶችን ለማምጣት እየጣሩ ነው፡፡ ይህ በሽታ እንደ ሌሎች የአእምሮ በሽታዎች ሁሉ በኅብረተሰቡ መጥፎ ስም የመስጠት ችግር ስላለ ሰዎች በግልጽ እርዳታ ለመጠየቅ እና የሚገባቸውን እንክብካቤ ለማግኘት አይጥሩም፡፡ 

Total Page Visits: 638 - Today Page Visits: 1

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *